January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የዓለማችን አጭሩ በረራ

አጠር ያሉ ጉዞዎች በመኪና፣ በአውቶቡስ እና በባቡር መደረጋቸው የተለመደ ነው።ዌስትሬይ እና ፓፓ ዌስትሬይ በሚባሉት የስኮትላንድ ደሴቶች መካከል የሚደረገው የአውሮፕላን ጉዞ የዓለማችን አጭሩ በረራ በመሆን ተመዝግቧል።በደሴቶቹ መካከል ያለው ርቀት 2.7 ኪሎ ሜትር ሲሆን፤ ነዋሪዎች ከአንዱ ደሴት ወደ ሌላው ለማምራት ሁለት አማራጮች እንዳሏቸው ተገልጿል።በጀልባ መጓዝ አንዱ አማራጭ ሲሆን፤ ሌላኛው እና በነዋሪዎቹ ተመራጭ የሆነው አነስ ባለ አውሮፕላን የአየር ጉዞ ማድረግ ነው።የአየር ላይ ጉዞው 2 ደቂቃን እንደሚፈጅ የተገለፀ ሲሆን፤ ጥሩ የአየር ሁኔታ ካለ ከዚያም ሊያንስ እንደሚችል ነው የተገለፀው።ከ17 እስከ 45 ዩሮ የሚያስከፍለው ይህ ጉዞ በክረምት ወቅት ብዙ ቱሪስቶችን እንደሚስተናግድም ተገልጿል።