November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ተረጂነትን ለማስቀረት አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅበታል ተባለ

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በማልማት ተረጂነትን ለማስቀረት የጀመረችውን ግብ ለማሳካት አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተወያዩ ነው፡፡በውይይቱም ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባ በአጽንኦት ተገልጿል፡፡የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እንደ ሀገር ያሉ እምቅ ሃብቶችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ተረጂነትን ማስቀረት እንደሚቻልም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም የልማት ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡የሀገር ሉዓላዊነት ምልዑ የሚሆነው የተረጂነት አስተሳሰብን በማስወገድ እና ምርታማነትን በእጅጉ በማሳደግ ራስን የመቻል ግብ ሲረጋገጥ መሆኑን አመላክተው÷ ከዚህ አኳያ አመራሩ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።የዛሬው ውይይት ዓላማም አመራሩ ከተረጂነት ለመላቀቅና ምርታማነትን ለማሳደግ የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ መግባባት ለመፍጠር ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

FBC

You may have missed