January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጀርመን ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቷን ያረጋገጠች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች

በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ 2ኛ መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል። በምድብ 1 አዘጋጇ አገር ጀርመን ከሀንጋሪ ጋር ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በስቱትጋርት አሬና ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ በጀርመን 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።ለጀርመን የማሸነፊያ ግቦቹን ሙሲያላ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ጉንዶጋን ከረፍት መልስ ከመረብ አሳርፈዋል።ጀርመን በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ ስኮትላንድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፏ ይታወሳል።እናም የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ጀርመን ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቷን ያረጋገጠች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።ጀርመን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን እሁድ ከስዊዘርላንድ ጋር የምታደርግ ሲሆን፤ ሀንጋሪ በበኩሏ ከስኮትላንድ ጋር ትጫወታለች።

EBC