January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በብሪክሱ መድረክ ተባብሮ የመስራት ችሎታዋንና ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን ማስመስከር ችላለች

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግቶ መቆየቱ ይታወቃል።ጽ/ቤቱ ሰኔ 11፣ 2016 ዓ.ም ዳግም አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፤ በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፓስፖርት ማደስ፣ የጠፋ ፓስፖርት መተካት እና የተበላሸ ፓስፖርት እርማት መስጠት ናቸው።በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ፓስፖርታቸውን ሲያሳድሱ የነበሩ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የቅርንጫፉ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት አዲስ አበባ ድረስ ለመሄድ ይገደዱ እንደነበር ገልጸዋል።በዚህም ለአላስፈላጊ እንግልት ተዳርገው እንደነበር ጠቅሰው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዳግም ስራ በመጀመሩ መደሰታቸውን መግለጻቸውን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

FBC