November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የ2016 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የ2016 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከናወን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መርሐ-ግብሩን ያዘጋጁት÷ የሰላም ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የትምህርት ሚኒስቴር መሆናቸው ተጠቁሟል።

የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የማዕድ ማጋራት፣ ትምህርትና የጤና አገልግሎት፣ አቅመ ደካሞችን መደገፍ ጨምሮ በዘንድሮው መርሐ-ግብር በ14 መስኮች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ 40 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች እንደሚሳተፉ፤ በዚህም ከ21 ቢሊየን ብር በላይ የሚተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ እና ከ50 ሚሊየን በላይ ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተብራርቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2016 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ማስጀመራቸው ይታወሳል።

FBC

You may have missed