January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሮን ተጓዘ

በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ በዛሬው እለት ከጠዋቱ ሰዓት ላይ ወደ ካሜሮኗ ዱዋላ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማስተዋል ዋለልኝ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ለልዑካን ቡድኑ አሸኛኘት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ለልዑካን ቡድኑ መልካም ቆይታ እና ውጤት ተመኝቷል፡፡

EBC