በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት ሽኝት ተደርጓል።
በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተዘጋጁት 45 የሜዳ ላይ ተግባራት ኢትዮጵያ በ41ዱ የምትሳተፍ ሲሆን÷34 ሴት እና 43 ወንድ አትሌቶችም ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ ኦሊምፒክ ላሉ ውድድሮች መነሻ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶችን ለማብቃት ላደረገው ጥረት ሊመሰገን እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
የእያንዳንዱ አትሌት ምኞት ውጤት ማምጣትና ኦሊምፒክ ላይ መሳተፍ በመሆኑ እንደ አፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያሉት ውድድሮች ትልቅ መነሻ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ÷ አትሌቶች በቆዩበት የ15 ቀናት የልምምድ ጊዜ እርስ በርስ ለመተዋወቅ እንደረዳቸው ተናግራለች፡፡
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።