July 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በህዳሴው ግድብ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን የተመለከተ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሕዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄን (ዶ/ር) ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በውይይቱም የመገናኛ ብዙኃን ባለፉት ዓመታት ፕሮጀክቱ አሁን ላለበት ቁመና እንዲደር ስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ግድቡ እስከሚጠናቀቅ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሰረተ-ልማቶች እስከሚዘረጉ ድረስ መገናኛ ብዙኃን ቀሪ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

ተቋማቱ ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ሥራዎች ባለፈ የዓባይን ታሪክ፣ የግንባታ ሂደቱንና ለኢትዮጵያ ያለውን አስተዋፅዖ ለቀጣዩ ትውልድ ሠንዶ ማስተላለፍ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ይህም ቀጣዩ ትውልድ ዓባይን በልኩ እንዲረዳ፣ ከተረጅነት ተላቆ ነፃ ኢኮኖሚን መገንባት እንዲችል ብሎም በዲፕሎማሲው መስክ በንቃት እንዲሳተፍ ያግዛል ነው ያሉት፡፡

በአጠቃላይ ግድቡ ከሚኖሩት 13 ተርባይኖች አሁን ላይ ሁለቱ ኃይል እያመነጩ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

FBC