ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ዓለማችን 85 ቢሊዮን ዶላር ለኑክሌር ጦር መሳሪያዎች እንደዋሉ ዓለም አቀፉ የጸረ ኑክሌር ጦር መሳሪያ ኢንስቲትዩት ገልጿልየኑክሌር ጦርነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡ዋና መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ጀኔቫ ያደረገው ዓለም አቀፉ የጸረ ኑክሌር ጦር መሳሪያ ንቅናቄ ተቋም ባወጣው ሪፖርት ጅምላ ጨራሽ ለሆነው ኑክሌር ጦር መሳሪያ የሚወጣው በጀት በ10 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡በዓለማችን በአጠቃላይ ካሉት 12 ሺህ 121 የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች መካከል 9 ሺህ 585 ያህሉ ለውጊያ ዝግጁ ተደርገው መቀመጣቸውን ይሄው ተቋም በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡ለውጊያ ዝግጁ ከተደረጉት መካከልም 3 ሺህ 904ቱ በሚሳኤል ላይ የተገጠሙ ናቸው የተባለ ሲሆን ይህም ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለአውዳሚ ጦርነት ተጋልጣለችም ብሏል፡፡ዓለምን ደጋግመው ማውደም ይችላሉ የሚባሉት የሩሲያ ኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ቁልፍ በማን እጅ ነው?የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቁ ዘጠኝ የዓለማችን ሀገራት በያዝነው ዓመት ውስጥ 85 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገዋል የተባለ ሲሆን አሜሪካ፣ ቻይና እና ሩሲያ ዋነኞቹ ሀገራት ናቸው፡፡ለኑክሌር ጦር መሳሪያ ወጪ ከተደረገው ጠቅላላ ገንዘብ ውስጥ አሜሪካ 80 በመቶ ድርሻ ሲኖራት ቻይና 11 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ሩሲያ 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገዋል ተብሏል፡፡ሕንድ፣ ፓኪስታን እና ሰሜን ኮሪያ የተጋነነ የደህንነት ስጋት ባይኖርባቸውም ያላቸውን ኑክሌር ጦር መሳሪያ ለውጊያ ዝግጁ ማድረጋቸው ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡በኑክሌር አረር ብዛት የዓለማችን ቀዳሚ የሆነችው ሩሲያ ተጨማሪ 36 ያህሉን ለውጊያ ዝግጁ ማድረጓ አሳሳቢ ነው የተባለ ሲሆን ሀገራት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ጦርነት ስጋት ላይ እንደወደቀች ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኑክሌር ጦር የታጠቁ ሀገራት ከመነጋገር ይልቅ ከውይይት መድረኮች እየራቁ ወደ ፉክክር መግባታቸው እንደሆነም ተቋሙ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም