ስምንት ወራትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ወደ ተኩስ አቁም እንዲያመራ የተጀመረው አለምአቀፍ ጥረት እስካሁን አልተሳካምየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ስድሰት አባላት ያሉትን የጦር ካቢኔ በመተናቸውን የእስራኤል ባለስልጣናት ተናግረዋል።ኔታንያሁ ካቢኔውን የበተኑት የመሀል ፓለቲካ አራማጁ የቀድሞ ጀነራል ቤኒ ጋንዝ ከካቢነው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው።ኔታንያሁ አሁን ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአብ ጋላንት እና በካቢኔው ውስጥ የነበሩት የስትራቴጂክ ጉዳይ ሚኒስትር ሮን ደርመር ካሉበት የሚኒስትሮች ቡድን ጋር ስለጋዛው ጦርነት እንደሚመካከሩ ተገልጿል።የፋይናንስ ሚኒስትሩ ቤዛሌል ስሞትሪች፣ የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን ጊቪር እንዲሁም ብሔርተኛ እና ሀይማኖታዊ የሆኑት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አጋሮች በጦር ካቢኔ ውስጥ ለመካተት ጥያቅ እያቀረቡ ናቸው። የጦር ካቢኔው የተቋቋመው ባለፈው ጥቅምት ወር የጋዛው ጦርነት ሲጀመር ተቃዋሚው ቤን ጋንዝ በሀገራዊ ጥምር መንግስት ውስጥ ከኔታንያሁ ጋር አብረው ለመስራት ከተስማሙ በኋላ ነበር።ጋንዝ ከጥምር መንግስቱ የወጡት ኔታንያሁ ለጋዛ ጦርነት ስትራቴጂ መንደፍ አልቻሉም የሚል ምክንያት በመስጠት ነው።ስምንት ወራትን ያስቆጠረው የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ወደ ተኩስ አቁም እንዲያመራ የተጀመረው አለምአቀፍ ጥረት እስካሁን አልተሳካም።
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች