November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 50 ሚሊየን ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለጸ

በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 50 ሚሊየን ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመላከተ፡፡የአገልግሎቱ ንቅናቄ የፊታችን ረቡዕ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በይፋ እንደሚጀመር የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ከ39 ሚሊየን በላይ በጎ ፈቃደኞች በሚሳተፉበት በዚህ መርሐ-ግብርም 50 ሚሊየን ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመላክቷል፡፡ኢትዮጵያዊ አብሮነትን እንደሚያጠናክር የተገለጸው ይህ ንቅናቄ በሦስቱ ተቋማት ቅንጅት በየደረጃው ይወርዳል ተብሏል፡፡“በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው በዚህ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 14 የስምሪት ዘርፎች መኖራቸውም ተብራርቷል፡፡የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለትምህርት ተደራሽነት የሚያበረክተውን የጎላ ሚና በመገንዘብ 20 ሺህ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ እንደሚሳተፉም ነው የተገለጸው፡፡

You may have missed