1445ኛው የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይል አስታውቋል፡፡የኢድ ሶላት በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በታደሙበት እጅግ በደመቀና በዓሉን በሚመጥን ሃይማኖታዊ ሥርዓት መጠናቀቁን ነው የጋራ ግብረ-ሃይሉ የገለጸው፡፡በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስቀድሞ የተደረገውን ዝግጅት የሚመጥን የተግባር አፈፃፀም ላሳዩ መላው የፀጥታ አካላትን አመስግኗል፡፡እንዲሁም ለበዓሉ ሠላማዊነት ለፀጥታ ሐይሉ ሥራ ተባባሪ በመሆን የድርሻቸውን ለተወጡ የዕምነቱ ተከታዬችና ለሰላም ወዳዱ የከተማው ነዋሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል ምስጋና አቅርቧል፡፡የጋራ ግብረ-ሃይሉ ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሠላም፣ የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።