የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ ባለፉት 10 ወራት ንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትና ሳኒቴሽን ዘርፍ የተኛለ ስራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡በዚህም አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ72 ሚሊየን ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡“ግድቤን በደጄ” በሚል ፕሮጀክትም በድርቅ የሚጎዱ አካባቢዎች የዝናብ ውሃን በማሰባሰብ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስራ በስፋት መከናወኑንም ጠቁመዋል፡፡ይህም በቀጣይ በሌሎች አከባቢዎች እንሰዲሰፋ ይሰራል ነው ያሉት፡፡ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ በተለያዩ ተቋማት ሲመሩ የነበሩ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ አግባብ መምራት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት በፍጥነት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡በዚህም ከውሃና ኢነርጂ ዘርፍ በተጨማሪ ከግብርና እንዲሁም ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት በመስራት ያለውን ሃብት በውጤታማነት መጠቀም መቻሉን ገልጸዋል።ለአብነት በተንዳሆ ግድብ ላይ በቅንጅት በተሰራው ህብረተሰቡን የመስኖ ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በውጤታማነት ጎርፍ የመከላከል ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡በዚህም መንግስት ያወጣው የነበረውን ተጨማሪ ወጪ ማስቀረት ተችሏል ነው ያሉት፡፡በቀጣይም ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ለኢዜአ ተናግረዋል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።