ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች 14 ጎሎችን በማስቆጠር ይመራል
ፈረንሳዊው አማካይ ሚሸል ፕላቲኒ ደግሞ በአምስት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን በማስቆጠር ይከተላል
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ በባየር ሙኒክ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም አዘጋጇ ጀርመን ከስኮትላንድ ጋር በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል።
ከአለም ዋንጫ ቀጥሎ ተጠባቂው አህጉራዊ ውድድር የአውሮፓ ከዋክብትን ያገናኛል።
ከ2004 ጀምሮ በአምስት የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች የተሳተፈው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ39 አመቱም ሌላ አዲስ ክብረወሰን ለማስመዝገብ ከፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ጋር ጀርመን ይገኛል።
ሮናልዶ በአምስት የአውሮፓ ዋንጫ መድረኮች በመሳተፍና ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ ሲሆን፥ በ14 ጎሎች 64 የሞላው ውድድር የምንጊዜው ጎል አስቆጣሪ ነው።
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አንድ አመት ዘግይቶ በተካሄደው ያለፈው የአውሮፓ ዋንጫ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር የወርቅ ጫማ የተሸለመው ሮናልዶ፥ በአውሮፓ ዋንጫ (ማጣሪያዎችን ጨምሮ) 45 ጎሎችን በማስቆጠርም ቀዳሚ ነው።
ፈረንሳዊው አማካይ ሚሼል ፕላቲኒ በአምስት ጨዋታዎች ብቻ ዘጠኝ ጎሎችን በማስቆጠር ሮናልዶን ይከተላል።
በ1984 ሀገሩን ሻምፒዮን ያደረገው ፕላቲኒ በውድድሩ ታሪክ ከአንድ ጊዜ በላይ ሃትሪክ በመስራት (ሁለት) የያዘው ክብረወሰን እስካሁን አልተሰበረም።
በአውሮፓ ዋንጫ በርካታ ጎሎች ያስቆጠሩትን ተጫዋቾች ይመልከቱ፦
Al-Ain
More Stories
በኤፍ ኤ ካፕ 4ኛ ዙር ድልድል ሩበን አሞሪም ከሩድ ቫን ኔስትሮይ አገናኝቷል
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞች መካከል የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ