የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የችግሩ አሳሳቢነት ግን እየከፋ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
የመንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በምክክር መድረኩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ÷በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወትን በመቅጠፍ፣አካል በማጉደል እና ንብረትን በማውደም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የችግሩ አሳሳቢነት ግን እየከፋ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ይህን ችግር ለመከላከል በቅንጅት በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በውይይቱ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የመንገድ ደህንነት ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ሲሆን÷ የትራፊክ አደጋን መከላከል ያልተቻለባቸውን ምክንያቶች በመለየት መሠራት ያለባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች እንደሚቀመጡ ተገልጿል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።