July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጡንቻዎቻችንን እንቅስቃሴ ወደ ንግግር የሚቀይር ቴክኖሎጂ ተሰራ

ፈጠራው በስራ ብዛት እና ድካም ምክንያት መናገር ላልቻሉ ሰዎች ሁነኛ መፍትሔ ይሆናል ተብሏል

በዩንቨርሲቲ መምህር የተሰራው ይህ ፈጠራ አንገት ላይ ከተገጠመ በኋላ የጡንቻዎቻችንን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ንግግር ማድረግ እንደሚያስችል ተገልጿል

የጡንቻዎቻችንን እንቅስቃሴ ወደ ንግግር የሚቀይር ቴክኖሎጂ ተሰራ፡፡

ፕሮፌሰር ጁን ቸን በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ዩንቨርሲቲ የባዮ ኢንጅነሪንግ ተመራማሪ ሲሆኑ ባንድ ወቅት ለረጅም ሰዓት ተማሪዎቻቸውን ካስተማሩ በኋላ ድካም ይሰማቸዋል፡፡

በወቅቱ የተሰማቸው ድካም ቀጣዩን ትምህርት ለተማሪዎቻቸው ማስተማር የማያስችል መሆኑን ተከትሎ ለዚህ ድካም መፍትሔ እንዲፈልጉ ለፈጠራው ምክንያት እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ድካም የተሰማው ሰው ድምጽ ሳያወጣ የጡንቻዎችን እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ በራሱ መናገር የሚያስችል ቴክኖሎጂ መፈጠር አለበት ያሉት እኝህ ተመራማሪ በመጨረሻም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ተጠቅመው ተሳክቶላቸዋል ተብሏል፡፡

እንደ አዲሱ ፈጠራ ከሆነ አንገታችን በተለምዶ ጉሮሯችን ጋር የምትገጠም አነስተኛ እና የጡንቻችን እንቅስቀሴ ማንበብ እንድትችል ተደርጋ የተሰራች ናት፡፡

ይህች የጡንቻችንን እንቅስቃሴ የምታነብ አነስተኛ ቁስ ለመስራት የግድ ባትሪ እንደማትፈልግም ተገልጿል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ ጆርናል ላይ የወጣው ይህ አዲስ ፈጠራ 7 ነጥብ 2 ግራም የምትመዝን ራሷን በራሷ የምታስነሳው ደቃቅ ማሽን በድካም ምክንያት አልያም ድካም ለመቀነስ በሚል በድምጽ መናገር ያልቻሉ ሰዎችን ታግዛለች፡፡

FBC