የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በተሰሩ ስራዎች እስካሁን 620 ሀገራዊ የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ስርዓት ማስገባት መቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጥ ሞላ (ዶ/ር)÷ የዲጂታል ስትራቴጂና ፖሊሲ ተቀርጾ የመንግስትን ተቋማት አገልግሎት ወደ ኤሌክትሮኒክ ወይም ዲጂታል ስርዓት ለማስገባት ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ገልጸዋል።
እስካሁን 620 ሀገራዊ የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል ስርዓት እንደገቡ መደረጉን አስረድተው፤ በቀጣይም የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ስርአት የማስገባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ቴሌኮምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሀገራዊ የዲጂታል እንቅስቃሴ ከፍተኛ እምርታ የመጣበት መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም ከ6 ትሪሊየን ብር በላይ የዲጂታል ፋይናንስ እንቅስቃሴ መደረጉን ተናግረዋል።
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ዕውን ለማድረግም በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሚኒስቴሩ በጤና፣ በማምረቻ፣ በግብርናና በሌሎችም ዘርፎች ችግር ፈች የሆኑ የምርምር ውጤቶች ተደራሽ የማድረግ እና ቴክኖሎጂ የማላመድ ስራዎችን ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ማከናወኑን ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የዲጂታል ክህሎት አቅም ለመገንባት በመጀመሪያ ዙር 10 ሺህ ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ ኤኒሼቲቭ መጀመሩን ገልጸው፤ በኢኒሼቲቩ እስከ 1 ሚሊየን ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።