July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሰኔ 30 ይካሄዳል- ፌደሬሽኑ

ሰኔ 16 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው 40ኛው የሻንበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ወደ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም መራዘሙን አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

በተመሳሳይ ከሰኔ 11 እስከ 15 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው 12ኛው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሰኔ 25 እስከ 29 ቀን እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ውድድሮቹ የሚካሄዱት በሐዋሳ ከተማ መሆኑን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፌደሬሽኑ ለሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አሥተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ተቋማት እና የግል ተወዳዳሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት÷ ምዝገባው እስከ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አስታውቋል፡፡

FBC