July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኮሊስትሮል መድሃኒትን የሰሩት ተመራማሪ ህይወታቸው አልፈ

ፔንስሊን ለተሰኘው መድሃኒት መገኘት መነሻ የሆኑት ጃፓነዊ ተመራማሪ በ90 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ

ተመራማሪው በህክምና ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የኖቤል ሽልማት አለመሸለማቸው ብዙዎችን አስቆጭቷል

የኮሊስትሮል መድሃኒትን የሰሩት ተመራማሪ ህይወታቸው አልፈ፡፡

አኪራ ኤንዶ በ1933 በገጠራማው የጃፓን አካባቢ ተወልደው በመላው ዓለም ያሉ ህመምተኞች ፈውስ እንዲያገኙ ያደረጉ ተመራማሪ ነበሩ፡፡

ኤንዱ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ተመራማሪው በተለይም ከልብ ህመም ጋር ለተያያዙ ህመሞች የሚውለው ስታቲን የተሰኘውን መድሃኒት በማግኘት ይታወቃሉ፡፡

መድሃኒቱ በኮሊስትሮል መብዛት ምክንያት የደም ቧንቧ መጥበብ እና የልብ ምት አለመስተካከል ጋር በተያያዘ በሐኪሞች የሚታዘዝ መድሃኒት ነው፡፡

Al-Ain