January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካ ለዳርፉር ነጻነት እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቀች

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች የዳርፉር ነጻነትን ለማወጅ ኤል ፋሸር የተሰኘች ከተማን ለመቆጣጠር ውጊያ ጀምረዋል ተብሏል

የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ዓመት አልፎታል

አሜሪካ ለዳርፉር ነጻነት እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቀች፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ሱዳናዊያን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ግብጽ፣ ቻድ እና ኢትዮጵያ የተሰደዱ ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ለሞት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች ከሰሞኑ በዳርፉር ግዛት ካሉ ቦታዎች በብቸኝነት በሱዳን ጦር ቁጥጥርሰ ር በቆየችው ኤል ሻፈር ከተማ ለመያዝ ከባድ ውጊያ እያደረጉ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ቶም ፔሪሎ ለቢቢሲ እንዳሉት አሜሪካ በማንኛውም ሁኔታ ለዳፉር ነጻነት እውቅና አትሰጥም ብለዋል፡፡

ኤል ፋሸር በምዕራብ ዳርፉር ስር ካሉ አካባቢዎች ውስጥ በሱዳን ብሔራዊ ጦር ቁጥጥር ስር ያለች ከተማ ነች፡፡

ከተማዋ በርካታ ሱዳናዊን በጦርነቱ ምክንያት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው የተጠለሉባት ከተማ ስትሆን የረድኤት ድርጅቶች መቀመጫም ነበረች፡፡

FBC