ከ371 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከግንቦት 23 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 128 ሚሊየን ብር የገቢና 243 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት፡፡
ከተያዙት እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ቡና፣ መድሃኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ አደንዛዥ እፆችና ሌሎች እቃዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና አዋሽ ቅረንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ