በሸካ ዞን የ2016 ዓ.ም የክልል አቀፍ የሚንስትሪ ፈተና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ።
በፈተና ማስጀመርያው መረሐ_ግብር ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የመማር ማስተማር ምዘና ዘርፍና ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) እንዲሁም የመምህራን ማህበር ስርዓተ ፆታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ከበደን ጨምሮ ለሎችም ተገኝቷል።
የመማር ማስተማር ምዘና ዘርፍና ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) እንደተናገሩት እንደ ክልል ከ48 ሺህ በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች በዚህ ፈተና እንደሚቀመጡ ገልጸዋል።
ከዚህ በፍት ከነበረው ክፍተት በርካታ ልምድ የተወሰደበትና ሰፊ ዝግጅት የተደረገበት ፈተና መሆኑን የገለጹት ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊው ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ እንድወጣ በማሳሰብ ፈተናው በሁሉም አካባቢ በተመሳሳይ እንደተጀመረ ተናግረዋል።
የመምህራን ማህበር ስርዓተ ፆታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ከበደ በበኩላቸው ከዚህ በፍት በተማሪዎች ውጤት ላይ በተመዘገበው ውድቀት ምክንያት ሰፊ ርብርብ ተደርጓልና አሁንም በፈተናው ወቅት በተዘጋጁት ልክ በራሳቸው ብቻ ፈተናቸውን እንድፈተኑ ኩረጃን ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የሚጠየፉት የፈተና አሰፈጻሚ አካላት ጭምር መሆን አለባቸው ብለዋል።
በዞኑ ካሉት የፈተና ጣቢያዎች በማሻ ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ፈተናውን በይፋ ያስጀመሩት የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዓለሙ እንደተናገሩት እንደ ዞን በ79 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው መሰጠት መጀመሩን ተናግረው ፊፁም ሰላማዊ እንድሆን በዬ ደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ አካላትና በኮማንድ ፓስት አባላት እየተመራ እንደሚገኝ ተናግረዋል
ፈተናው ከኩረጃ የፀዳ እንድሆን ጥብቅ ክትትል እንምደረግ ያነሱት አቶ መስፍን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፍነቱን በተገቢው መንገድ በመወጣት በዘርፉ ጥሩ ውጤት እንድትመዘገብ ርብርብ እንድያደርጉም አሳስበዋል ።
ለተከታታይ ሁለት ቀን የሚቆየው ፈተና በሁሉም መዋቅሮች በተመሳሳይ ሰዓት የተጀመረ ሲሆን በማስጀመሪያ ላይ የዞን የከተማና የየወረዳ አመራር አካላትና የፈተና አስፈጻሚ አካላት ተገኝቷል።
ዘጋቢ ካሳሁን ደንበሎ
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።