January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢራን ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎችን ይፋ አደረገች

የኢራን የሀገርውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ 6 እጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ በዚህ ወር በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የስድስት እጩዎችን የመጨረሻ ዝርዝር ነው ይፋ ማድረጉ የተሰማው፡፡

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በቅርቡ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ በሄሊኮፍተር አደጋ ህይዎታቸው ማለፉን ተከትሎ ለሀገሪቱ አዲስ ፕሬዚዳንት መምረጥ በማስፈለጉ ነው የሚካሄደው፡፡

ለፕሬዚዳንትነት ከሚወዳደሩት እጩዎች መካከል በሀገሪቱ በምክትልፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙትን አሚርሆሴይን ቃዚዛዴህ ሃሺሚን ን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች እያገለገሉ ያሉ ሃላፊዎች እንደሚገኙበት የአርቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

FBC