በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 875 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ፥ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 18 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ39 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተጠቁሟል፡፡
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ