January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ3 ዶላር ቤት እየሸጠች ያለችው የጣሊያን ከተማ

በነዋሪዎች እጥረት የተቸገረችው የጣሊያኗ ሳምቡካ ዲሲሲሊያ ከተማ ነዋሪዎችን ለመሳብ ለሶስተኛ ዙር ቤቶችን ለጨረታ አቅርባለችቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትልዩልዩበ3 ዶላር ቤት እየሸጠች ያለችው የጣሊያን ከተማበነዋሪዎች እጥረት የተቸገረችው የጣሊያኗ ሳምቡካ ዲሲሲሊያ ከተማ ነዋሪዎችን ለመሳብ ለሶስተኛ ዙር ቤቶችን ለጨረታ አቅርባለችአል-ዐይን 2024/6/8 16:58 GMTከዚህ ቀደም በሁለት ዙር በወጣ የቤት ሽያጭ 250 ቤቶች ተሸጠዋልየበርከታ ወና ቤቶች መገኛ የሆነችው የሲሲሊያዋ ሳምቡካ ከተማ ሶስተኛ ዙር የቤት ጨረታ ማስታወቂያ አስነግራለች፡፡ ከ3 ዶላር አልያም በ171 ብር ጀምሮ ቤቶችን ለሽያጭ ያቀረበችው ከተማዋ በ2019 እና 2021 ተመሳሳይ ቤቶችን ጨረታ አውጥታ ነበር፡፡ከ50 እስከ 80 ስኩየር ሜትር ላይ ያረፉት ቤቶች ባለሁለት እና ሶስት ፎቆች ሲሆኑ ቤቶቹ ከአንድ እስከ ሶስት መኝታ ቤቶችን ያያዙ ናቸው።በ1969 በከተማዋ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው በመውጣታቸው የተነሳ የነዋሪዎች ቁጥር እየተመናመነ በመምጣቱ በርካታ መኖርያ ቤቶች ያለሰው ተዘግተው ይገኛሉ፡፡የሳምቡካ ከተማ አዲስ ከንቲባ ጁሴፔ ካሲዮፖ ባለፉት አመታት የወጡት የቤት ሽያጮች ግዙፍ የሪልስቴት አልሚዎችን እና ነዋሪዎችን መሳብ እንደቻሉ ተናግረው በቀጣይ አመታትም በተመሳሳይ ቤቶቹን ለሽጭ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡በ2019 እና በ2021 ለጨረታ በቀረቡ ቤቶች የከተማዋ መዘጋጃቤት 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኝት ችሏል፡፡የጣሊያን መንግስት ሳምቡካን ጨምሮ በደቡባዊ ሮም የምትገኝው ፓትሪሲያ ከተማ ያወጡትን የቤት ጨረታ ማስታወቂያ የደገፈ ሲሆን ቤቶች በከተሞቹ ማዘጋጃቤቶች ተይዘው ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃገብነት ሽያጩ እንዲቀጥል ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ጥንታዊ ይዘት ያላቸው መኖርያ ቤቶቹ አሁን ባሉበት ሁኔታ ለመኖርያነት ምቹ ሲሆኑ የቤቱ ገዥ በቅንጡ ሁኔታ እድሳት ማድረግ ቢፈልግ ከ32 ሺህ እስከ 200ሺ ዶላር ብቻ ወጪ በማድረግ ዋጋቸውን ከፍ በማድረግ መሸጥ ይችላል ነው የተባለው፡፡ከዚህ ቀደም በነበሩት ሽያጮች ከአንድ ሺህ እስከ 25ሺህ ዩሮ ድረስ ቤቶቹ የጨረታ መነሻ ተቆርጦላቸው ለገበያ የቀረቡ ሲሆን ቤቶቹ በአማካኝ 5ሺህ ዩሮ መሸጣቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

Al-Ain