January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአፋር ክልል የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢጃራ ተስፋዬ የተንዳሆ እና አላሎ ባድ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ጎብኝተው ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡የጉብኝቱ ዓላማ ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ችግር ለመፍታትና ወደ ስራ ለማስገባት መሆኑን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡በሚቀጥለው ዓመት ለፕሮጀክቶቹ በጀት በመመድብ ጥገና በማድረግ ወደ ስራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።በተያያዘ በሰመራ ከተማ የሚገኘውን የኢንስቲትዩቱ ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታም ተመልክተዋል።

FBC