አብያተ ክርስቲያናቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበሩ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት እንዲሰረዝ መወሰኑን አስታወቀ።
ካውንስሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ዙሪያ የ3ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ካውንስሉ በመግለጫው የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩትን በመለየት አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ መቆየቱን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ የካውንስሉን ምክር ተቀበለው፤ ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ያልተገኙ አራት አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት እንዲሰረዝ መወሰኑን አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት
1 ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ
ነቢይ ኢዮብ ጭሮ
2 ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን
መጋቢ ካሳ ኪራጋ
3 የሰማይቱ ጽዮን ማኀበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን
መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ
4 የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ
መጋቢ ቢኒያም ሽታዬ
ስማቸው የተቀመጡ አካላት ከዚህ ቀደም ከነበረባቸው ስህተቶች እንዲታረሙ ቢመከሩም ፈጽሞ ሊመለሱ ያልቻሉ መሆናቸው ታውቆ ካውንስሉ ለሚወስደው ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ የሚመለከተው የመንግስት አካል ድጋፍ እንዲያደርግለትም ጠይቋል።
በቀጣይ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ ስም የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦችና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ሁሉ ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አስመልከቶ ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ድጋፍ እንዲረግለትም ካውንስሉ ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪም ካውንስሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለወንጌል እና ለእግዚአብሔር ቃል የቀኑ በማስመሰል ኢ/መጽሃፍ ቅዱሳዊ የሆነ ተግባር የሚፈጽሙና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተሰማሩ ግለስቦች ላይ አስፈላጊው የህግ የእርምት እርምጃ ወስዶ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
Al-Ain
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)