ባህላዊ ዕሴቶችን ጠብቆ በማልማትና ለትውልድ ተሻጋሪ ከማድረግ ባሻገር የኢኮኖሚ መሰረት እንዲሆኑ መስራት ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ም/ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡
ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ለቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) (ኢ/ር) በመልዕክታቸው ÷የቤንች ብሔረሰብ የራሱ የሆኑ ባህላዊ ዕሴቶች ያሉት መሆኑን አውስተዋል፡፡
እነዚህን ዕሴቶች በመጠበቅ ፣በመንከባከብ ፣በማልማትና ለትውልድ ተሻጋሪ ለማድረግ የቤንች ብሔረሰብ ብርቱ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
የብሔረሰቡ አባቶች ያቆዩትይህ በዓል ለአሁኑ ትውልድ መተላለፉ ትልቅ ሥራ በመሆኑ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት ይገባል ብለዋል።
ዕንቁ የሆነውን የቤንች ብሔረሰብ ባህላዊ ዕሴት በመንከባከብ ፣በመጠበቅና በማልማት መልካም ሥራዎች ላይ በማዋል ይበልጥ እየዳበረ እንዲሄድ መስራት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ወደ አዲስ ዓመት ሲገባ የተሻለ ለመስራት፣ በውጤት ለመገኘት፣አብሮነትንና አንድነትን ለማጠናከር ሁሉም መዘጋጀት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ በሚገኙ ብሔረሰቦች በርካታ መልማት የሚገባቸው ባህላዊ ዕሴቶች እንዳሉ ጠቁመው ÷እነዚህን ዕሴቶች በማጥናት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የክልሉ መንግስት አበክሮ ይሰራል ነው ያሉት።
ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣የመተሳሰብ ፣የአብሮነት እንዲሆንም መመኘታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
FBC
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)