የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማትና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ርስቱ ይርዳው በጎደር ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በተጨማሪም በክረምቱ ወራቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሊተከሉ የተዘጋጁ የዛፍና የፍራፍሬ ችግኞችን ዝግጅት በችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ተገኝተው እየተመለከቱ ይገኛሉ።
በከተማው የኢንዱስትሪ መንደሮች ጨምሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በወጭና በተኪ ምርቶች የተሰማሩ ባለሃብቶችን የምርት ሒደት እንደሚጎበኙም ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተስፋየ ይገዙ በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ የተለያዩ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን እየጎበኙ ነው።
በከተማው የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችና ሌሎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችንም እየጎበኙ መሆኑ ተመላክቷል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።