July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሶማሊያ ከ50 በላይ አመታት በኋላ የተመድ የጸጥታው ም/ቤትን ተቀላቀለች

ሶማሊያ ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ 15 አባላት ባሉት የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ለሁለት አመታት እንድታገለግል በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው እለት ተመርጣለች።

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝደንት “በሚስጥር በተሰጠው ምርጫ፣ የተመረጡት ሀገራት አስፈላጊውን የ2/3 አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል” ብለዋል

ሶማሊያ ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ 15 አባላት ባሉት የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ለሁለት አመታት እንድታገለግል በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው እለት ተመርጣለች።

ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሶማሊያ በተጨማሪ ዴንማርክ፣ ግሪክ፣ፓኪስታን እና ፓናማ መመረጣቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

“የሶማሊያ ከጸጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር መቀላቀሏ ተምሳሌታዊ እና ዲፕሎሜሲያዊ ጠቀሜቻዎች አሉት፤ ይህ ሶማሊያ ከአባል ሀገራት ጋር ለመተባበር ይረዳታል” ሲሉ ሶማሊያዊዉ ተንታኝ አብዲቀፋር አብዲ ዋርድሄር ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ተንታኙ እንደሚሉት ከሆነ ሶማሊያ በ50 አመታት በኋላ በአለም ዙሪያ ባሉ ግጭቶች ዙሪያ በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ ጽምጽ ይኖራታል።

“እንደ ጦር መሳሪያ ማዕቀብ መጣልን እና ኃይል መጠቀምን የመሳሰሉ አስገዳጅ ውሳኔ የሚሰጠው ብቸኛው የተመድ አካል የጸጥታው ምክርቤት ነው። ስለዚህ ሶማሊያ የአለም ጉዳዮችን የሚወስን ድምጽ ይኖራታል ማለት ነው።”

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝደንት ዴኒስ ፍራንሲዝ የምርጫውን ውጤት ባሳወቁበት ጊዜ “በሚስጥር በተሰጠው ምርጫ፣ የተመረጡት ሀገራት አስፈላጊውን የ2/3 አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል” ብለዋል።

ይህን ተከትሎ በሶማሊያ የሚገኘው ተመድ፣ ሶማሊያ በጸጥታው ምክርቤት ከ2025-2026 እንድታገለግል በመመረጧ ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የደስታ መልእክት አስተላልፏል።

“ሶማሊያ ባለፉት ሶስት አሰርት አመታት ከሰላም፣ ከጸጥታ እና ብልጽግና ርቃ ቆይታለች” ብለዋል የተመድ ዋና ጸኃፊ ልዩ መልእክተኛ ተወካይ ጀምሰ ስዋን።

ይህ በምክርቤቱ የተካሄደው ምርጫ በሶማሊያ  መሻሻል መኖሩን የሚያሳይ ነው ያሉት ስዋን ምክርቤቱ በአለም አቀፍ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ በሚያደርገው ውይይት ላይ የሶማሊያ ልምድ ተፈላጊ ነው ብለዋል።

የተመድ የጽጥታው ምክር ቤት 15 ያሉት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር ወይም ቬቶ ፓወር ያላቸው ብሪታኒያ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ እና አሜሪካ ቋሚ አባላት ናቸው።

Al-Ain