January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳውዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ልዑኩ በአዲስ አበባ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።በተጨማሪም የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎም ይጠበቃል።

EBC