January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

172 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

172 ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።ኤምባሲውና የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በትብብር በሦስት ዙር 172 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በዚህ ሣምንት በአውሮፕላንና በባቡር ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገልጿል። የኢትዮ-ጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በድንበር ተሻጋሪ ሕገ-ወጥ ቡድኖች ምክንያት ዜጎች ለድብደባ፣ እንግልት፣ ዘረፋ እንዲሁም ሞት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ኤምባሲው ባወጣው መረጃ አስገንዝቧል።ለዚህም ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከዚህ መሰል አደጋ ለመጠበቅ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የጋራ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

EBC