የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኳታር ዶሃ የሚገኘው የዶክ ሕክምና ማዕከል መስራች በሆኑት ዶ/ር ኢማኑኤል ቶሎሳ ከተመራ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል። የሕክምና ማዕከሉ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በኢንቨስትመንት መሰማራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል።ማዕከሉ በዓይነቱ ልዩ የሆነ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአጥንት ህክምና ማዕከል በኢትዮጵያ ለማቋቋም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል። ዶክ በኳታር ከኦርቶፔዲክ፣ ሩማቶሎጂ፣ ኒውሮሎጂ፣ ኒውሮፊዚዮሎጂ፣ ፊዚዮቴራፒ፣ ካይሮፕራክቲክ እና የጥርስ ሕክምና ጋር የተያያዙ የምርምራ እና የሕክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ ትልቁ የጤና ማዕከል መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
EBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።