January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለይተው አጠናቀቁ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ ለ6ኛ ቀን ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

አምስቱ የምክክር ባለድርሻ አካላት ትናንት እና ዛሬ ከሰዓት በፊት በነበረው መርሐ-ግብር የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን በቡድን ሆነው ሲያጠናቅሩና ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡

ባለድርሻ አካላቱ ያጠናቀሯቸውን እና ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በቃለ-ጉባዔ በማዘጋጀት ለአጠቃላይ መድረኩ የሚያቀርቡላቸውን ተወካይ ግለሰቦችንም መርጠዋል፡፡

ዛሬ ከሰዓት በተካሄደው መርሐ-ግብር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቡድን ሆነው ተስማምተው ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ለጋራ መድረኩ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በሚኖረው መርሐ-ግብር የየባለድርሻ አካላቱ ወኪሎች ከሞደሬተሮች ጋር በመሆን የሁሉንም አጀንዳዎች በጋራ ሆነው አስቸኳይነትን፣ አስፈላጊነትን እና ወካይነትን ከግምት በማስገባት በየፈርጁ ያደራጃሉ፡፡

በነገው ዕለትም በየፈርጁ የተደራጁት አጀንዳዎች የአዲስ አበባ ከተማ አጀንዳ ሆነው ለምልዓተ ጉባኤው ከቀረቡ በኋላ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተገኙበት የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

FBC