
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፥ ለፈጠራ ሀሳብና ለምርምር ምቹ የሆነ የስራ ከባቢ እንዲፈጠር ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተከናወኑ የልማት ስራዎችና የኢኖቬሽን ውጤቶችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፥ በኢንስቲትዩቱ ለፈጠራ ሀሳብ ማፍለቂያ እና ለምርምር ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል።ኢንስቲትዩቱ ከሀገር የልማት ግብ አኳያ ብቁ ሙያተኞችን እያሰለጠነ እንዲሁም በፈጠራና በእውቀት የሚመራ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያወጣ ነው ብለዋል።በየዓመቱ 10 ሺህ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ፤ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂስቶች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱንም መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሳካ ብቁ የሰው ኃይል ስልጠና እና ምርምር ዋነኛ ትኩረታችን ነው ብለዋል።በዚህም የኢትዮጵያን ግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮንስትራክሽንና ሌሎች ዘርፎችን ይበልጥ የሚያዘምኑ በርካታ ቴክኖሎጂዎች በኢንስቲትዩቱ መፈጠራቸውን አንስተዋል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።