January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ዓመት የሚጠበቀው ላሊና የተሰኘ የአየር ንብረት ለውጥ ለዓለማቀፍ የአየር መቀዝቀዝ ሚና እንደሚኖረው አስታወቀ።

የ«ላ ሊና »መከሰት ለወራት የዘለቀውን ሙቀት መጠን ሊቀንስ እንደሚችል መተንበዩን የተመድ የአየር ትንበያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ከጎርጎርሳውያኑ 2023 አጋማሽ ጀምሮ ኤል ኒኖ ያስከተለው የዓለም ሙቀት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አስከፊ የአየር ሁኔታ እንደከሰት አድርጓል ያለው ዘገባው የ«ላ ሊና» የዓየር ለውጥን ተከትሎ መቀዛቀዝ እያሳየ መምጣቱን ገልጿል። በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ውስጥም እመርታዊ ለውጥ ሊያሳይ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት ተንብዪዋል።
ትንበያው እንደሚያሳየው ምንም እንኳ በ«በላ ሊና» ክስተት ሙቀቱ በጊዜያዊነት መቀዛቀዝ ቢያሳይም የሰው ልጅ በሚያስከትለው የአየር ንብረት ለውጥ መዘዝ የዓለም ሙቀት እየጨመረ መሄዱ እንደማይቀር ነው። ይህንኑ ተከትሎም የተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ወቅቱን ላልጠበቀ ዝናብ እና ሙቀት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ነው ዘገባው ያመለከተው።
የውቅያኖስ አካባቢዎችን ሙቀት እንደሚቀንስ ተስፋ የተጣለበት «ላ ኒና » በዋናነት ከነፋስ፣ ከዝናብ እና ከከባቢ አየር ግፊት ለውጥ ጋር ተዳምሮ በሞቃታማው የፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢዎች ውስጥ ያለውን የሙቀት መጠን እንደሚያቀዘቅዝ ይጠበቃል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዘገባ እንደሚያመለክተው ላ ሊና ከፊታችን ከሐምሌ እስከ መስከረም ባሉ ወራት የአየር ሁኔታዉን 60 ከመቶ እንዲሁም ከነሐሴ እስከ ህዳር ባሉ ወራት ደግሞ 70 በመቶ የመከሰት ዕድል አለው።

DW