ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ዓ.ም ለ100 ቀናት ንባብን ሲያበረታታ መቆየቱን ገልጸው፤ ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 24ኛ ዓመት የኤፍኤም አዲስ 97.1 የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማንበብ ባህል፣ መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን ሲሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የንባብ ባህልን ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን ብለዋል።
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ