January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቢሳው አቀና

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ መዲናዋ ቢሳው ተጉዟል።

23 ተጫዋቾችን ያካተተው ልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ በቶጎ (ሎሜ) አድርጎ ቢሳው ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ወደ ጊኒ ቢሳው ከማምራቱ አስቀድሞ የመጨረሻ የሀገር ቤት ልምምዱን ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ማከናወኑ ተገልጿል።

FBC