ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ መክፈቻ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም አቀፉ ስታርትአፕ አዋርድስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኪም ባልና የተለያዩ ስታርትአፕ ተወካዮች ተገኝተዋል።
መርሐ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ ስታርትአፕ አዋርድስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን÷ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ተባባሪ አዘጋጅ ነው።
የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ስታርትአፖች ተወዳድረው ለአሸናፊዎቹ ሽልማት እንደሚሰጥ የዘገበው ኢዜአ ነው።
በዛሬው መርሐ ግብር ኢትዮጵያን ወክለው በምስራቅ አፍሪካ የግሎባል ስታርትአፕ አዋርድስ የሚሳተፉ ስታርትአፖች ይፋ ይሆናሉ።
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።