ላለፉት አንድ መቶ ቀናት በተካሄደው የንባብ ዘመቻ በቁጥር አንድ መቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።
የሃይማኖት ሰዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የስፖርት ሰዎች፣ የንግድና ሥራ ፈጣሪዎች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ የገዢ እና ተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ ሰዎችና ከሌሎች ዘርፎች የተወከሉ ዝነኞች የንባብ ልምዳቸውን አካፍለዋል፤ የምጊዜም ምርጥ መጽሐፎቻቸውንም ጠቁመዋል።
በመቶ ቀናቱ ቆይታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መጻሕፍት በዝነኞቹ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፎች እየተባሉ የተጠቆሙ ሲሆን፤ በርካታውን እጅ የሚይዙት የሀገር ውስጥ መጻሕፍት ናቸው።
በብዛት ከተጠቆሙ የሀገር ውስጥ መጽሐፎች፥ ነባር ልቦለዶች እንዲሁም የህይወት ታሪክና ግለ ታሪኮች ቅድሚያውን ወስደዋል። ከእነዚህም መካከል፦
- ፍቅር እስከመቃብር፣ በሀዲስ ዓለማየሁ (ብዙ ጊዜ ተደጋሞ የተመረጠ መፅሃፍ)
- ኦሮማይ፣ በበዓሉ ግርማ
- የህይወቴ ታሪክ (ኦቶባዮግራፊ)፣ በፊታውራሪ ተ/ሐዋርያት ተ/ማርያም
- እሳት ወይ አበባ፣ በጸጋዬ ገ/መድኅን
- የኤርትራ ጉዳይ፣ በአምባሳደር ዘወዴ ረታ
- መጽሐፈ ትዝታ ዘዓለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ፣ በመንግሥቱ ለማ
- ትዝታ፣ በሀዲስ ዓለማየሁ
- ህይወቴ፣ በደጃዝማች ወ/ሰማያት ገ/ወልድ
- የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ፣ በእጓለ ገ/ዮሐንስ
- ህይወቴና የኢትዮጵያ ርምጃ፣ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላ
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።