ጃፓን የምግብን ጣዕም በራሱ ጊዜ የሚመጥን ዘመናዊ ማንኪያ ሰራች ቴክኖሎጂው በተለይም ከጨው ጋር በተያያዘ ችግር ላለባቸው ሰዎች ፍቱን መድሃኒት ነው :: በቻርጅ የሚሰራው ይህ ማንኪያ በ28 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ጃፓን የምግብን ጣዕም በራሱ ጊዜ የሚመጥን ዘመናዊ ማንኪያ ሰራች፡፡የጃፓኑ ኪሪን ሆልዲንግስ የቴክኖሎጂ ተቋም በኤሌክትሪክ የሚሰራ የምግብ ጣዕም ማጣፈጫ ማንኪያ ሰርቻለሁ ብሏል፡፡ኩባንያው እንዳለው ከሆነ ከሁለት ዓመት በፊት ጨው ያነሳቸው ምግቦች ላይ ጨው በራሱ መጨመር የሚያስችል ማንኪያ ሰርቶ እንደነበር ገልጿል፡፡ይሁንና ጨው አብዝቶ መውሰድ ለሰው ልጆች ጤና ጉዳት ያለው መሆኑን ተከትሎ ፈጠራውን ወደ ማሻሻል መግባቱን ኩባንያው አስታውቋል፡፡በዚህም መሰረት በምግባችን ላይ አነስተኛ ጨው መጠን ኖሮ ነገር ግን በምላሳችን ላይ ግን የጨው መጠኑ የተስተካከለ እንዲመስል የሚያደርግ ማንኪያ ለተጠቃሚዎች ዘግጁ ሆኗል ተብሏል፡፡ይህ ማንኪያ አንድ ጊዜ ከተገዛ በኋላ በኤሌክትሪክ ቻርጅ በማድረግ በየጊዜው መጠቀም እንደሚቻል ተደርጎ ስለመሰራቱም ኩባያው ገልጿል፡፡አንዱ የምግብ ጣዕም ማመጣጠኛ ማንኪያ በ19 ሺህ 800 የጃፓን የን ወይም በ28 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል፡፡
Al-Ain
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ