January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሪያል ማድሪድ 15ኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫውን አነሳ

ካርሎ አንቸሎቲ አምስት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ያነሱ አሰልጣኝ በመሆን አዲስ ታሪክ አጽፈዋልሪያል ማድሪድ የጀርመኑን ቦርሺያ ዶርትሙንድ በማሸነፍ 15ኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫውን አነሳ።ማድሪድ በምሽቱ የዌምብሌይ የፍጻሜ ጨዋታ ዳኒ ካርቫሃል በ74ኛው፤ ቪንሺየስ ጁኒየር በ83ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ለድል የበቃው።የኤዲን ቴርዚች ቡድን በመጀመሪያው አጋማሽ የፈጠራቸውን የጎል እድሎች መጠቀም አለመቻሉ ዋጋ አስከፍሎታል።በተለይ ካሪም አድየሚ ሁለት የጎል እድሎችን ያመከነበት አጋጣሚ በድጋፍ ድምጻቸው ዌምብሌይን ላደመቁት የዶርትሙንድ ደግፊዎች የሚያስቆጩ ነበሩ።

Al-Ain