በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው። ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም።ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው። ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል። ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለሀገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው። ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል።1. ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል2. ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባህል እንዲሆን ያደርጋል3. በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል። ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል። በመሆኑም ይኽንን እድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለሁ።›› – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።