November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች ያለቀላቸው ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በስፋት እየተመረቱ ነው ተባለ

በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች ያለቀላቸው ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በስፋት እየተመረቱ ነው ተባለOn Jun 1, 2024  74አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን በመጠቀም ያለቀላቸው ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በስፋት እንዲመረቱ እየተደረገ መሆኑን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ።በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት “የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት እሴት ሰንሰለት በአፍሪካ” በሚል ሃሳብ ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ እንደገለጹት ፥ በተለይም የ”ኢትዮጵያ ታምርት”ንቅናቄ በራስ አቅም አምርቶ ራስን ለመቻል አቅም ሆኗል።ባለፉት ዓመታት በትንሹ በዓመት አንድ ቢሊየን ዶላር የሚሆን የውጭ ምንዛሪ በማውጣት የጨርቃ ጨርቅና የአልባሳት ምርቶች ሲገቡ መቆየታቸውን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።አሁን ላይ በራስ አቅም በማምረት ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው ፥ የሀገር ውስጥ ጥሬ እቃዎችን በመጠቀም ያለቀላቸው ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በስፋት እየተመረቱ መሆኑን ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት እየተገኙ ያሉ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልም በዘርፉ የተገኙ ውጤቶች ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል አቶ ስለሺ።

FBC