November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ ሆነ

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከ14 የምርጫ ክልሎች የሰበሰበውን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚሁ መሰረት ገዢው ፓርቲ ኤኤንሲ 43 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሲመራ ዲሞክራቲክ አሊያንስ ፓርቲ ደግሞ በ26 በመቶ ድምጽ ይከተላል።በጁሊየስ ማሌማ የሚመራው ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ (ኢኤፍኤፍ) እና በደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የተመሰረተው “ኡምኮንቶ ዊሲዝዌ” ፓርቲ (ኤምኬ ፓርቲ) በተመሳሳይ 8 በመቶ ገደማ ድምጽ ማግኘታቸው ተጠቁሟል።የምርጫው የመጨረሻ ውጤት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። የቅድመ ምርጫ ትንበያዎች የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ከ30 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ ያለውን አብላጫ መቀመጫ ሊያጣ እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን ይህም ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግስት የመመስረት ግዴታ ውስጥ እንዲገባ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።

EBC