January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሚቀረፁ አጀንዳዎች የሴቶችን ጥያቄ ያማከሉ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፡- የጥምረት ለሴቶች ድምፅ ጽ/ቤት

የሚቀረፁ አጀንዳዎች የሴቶችን ጥያቄ ያካተቱ መሆን እንዳለባቸው በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከጥምረት ለሴቶች ድምፅ ጽሕፈት ቤት ተሳታፊ የሆኑት እየሩሳሌም ሰለሞን ተናገሩ።የማህበሩ ዋና ዓላማ ሴቶች በበቂ ሁኔታ በምክክሩ እንዲሳተፉ ማድረግ መሆኑንም ነው የገለፁት።ሴቶች በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም በፖለቲካው በበቂ ሁኔታ እና ቁጥር እንዲሳተፉ የተመቻቹ ሁኔታዎች አናሳ መሆናቸውንም ተናግረዋል።ተቋሙ በተለያዩ ክልሎች ያሉ ሴቶች ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ ማድረግ ቀዳሚ ስራው እንደሆነ እየሩሳሌም ተናግረዋል።

EBC