November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ተስማምተዋል፡፡የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ ኮርሪያ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡በቆይታቸውም÷ ከሀገሪቱ አቻቸው ቴዮንግ ቾ ጋር በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ ተገናኝተው በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ የስጋት ደረጃው እያደገ የመጣውን ሽብርተኝነትን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል፡፡ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውንም አገልግሎቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡ከዚህም ባለፈ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡በሁለቱ ሀገራት የመረጃና ደኅንነት ተቋማት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር በስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ በማጠናከር እና የመረጃ ልውውጥን በማሳደግ የጋራ የሆኑ ስጋቶችን ለመፍታት እንደሚሠሩም ተመልክቷል፡፡አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ ዘማቾች የተገነባውን የመታሰቢያ ሙዚዬም መጎብኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

FBC

You may have missed