July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የቱሪዝም ልማት ስራዎች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከጣሊያን አምባሳደር ኦገስቲኖ ፔልሲ ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በቱሪዝም ዘርፍ በጣሊያን መንግሥት ትብብር ስለሚከናወኑ ተግባራት ተነጋግረዋል።

አምባሳደር ኦገስቲኖ ፔልሲ፥ የጣሊያን መንግሥት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚያከናውናቸው የቅርስ እድሳት እና የቱሪዝም ልማት ስራዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ የሰው ኃይል ልማት ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት መደረሱን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

EBC