January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የልጁን ጾታ ለማወቅ በሚል የሚስቱን ሆድ ለመቅደድ የሞከረው ሰው የእድሜ ልክ እስር ተፈረደበት

የአምስት ሴት ልጆች አባት የሆነው አባወራው ወንድ ልጅ የመውለድ ከፍተኛ ጉጉት ነበረው ተብሏል

ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ሊወለድ አንድ ወር የቀረው ወንድ ልጅ በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ አልፏል

የልጁን ጾታ ለማወቅ በሚል የሚስቱን ሆድ ለመቅደድ የሞከረው ሰው የእድሜ ልክ እስር ተፈረደበት፡፡

ፓና ላል በህንዷ ኡታር ፕራዲሽ የሚኖር ሲሆን ላለፉት 22 ዓመታት አኒታ ከተሰኘች ሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡

ሁለቱ ባለትዳሮች አምስት ሴት ልጆችን ያፈሩ ቢሆንም አባትየው ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ሚስቱን ተጠያቂ ያደርግ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ስድስተኛ ልጃቸውን ሊወልዱ ትንሽ ቀናት የቀራቸው እነዚህ ባለትዳሮች በተለይም አባትየው የልጃቸውን ጾታ አጥብቆ ማወቅ ይፈልግ ነበር፡፡

የባልና ሚስት የቅርብ ቤተሰቦች ጉዳዩን በእርጋታ እንዲፈቱት ቢወተውቱም ጥንዶቹ ችግራቸውን መፍታት እንዳልቻሉ ተጠቅሷል፡፡

የልጁን ጾታ ለማወቅ እስኪወለድ የመጠበቅ ትዕግስት ያጣው ይህ አባትም የሚስቱን ሆድ ለመቅደድ ሲሞክር ሚስትየው ሮጣ ታመልጣለች፡፡

በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ወደ ሚሰራው ወንድሟ በመሄድ ላይ እያለች ህመም በርትቶባት ስትጮህ የሰማው ወንድሟም ወደ ሆስፒታል እንደወሰዳት እና ህይወቷ እንደተረፈ ኢንዲያን ቱዴይ ዘግቧል፡፡

Al-Ain