ሰሜን ኮሪያ 10 ገደማ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ጃፓን ባህር ክልል መተኮሷ ተነግሯል
ሰሜን ኮርያ ከ260 በላይ ፊኛዎችን ተጠቅማ ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ መላኳ ይታወቃል
ሰሜን ኮሪያ ለጎረቤቶቿ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ “የባላስቲክ ሚሳዔል እና የቆሻሻ” ስጦታዎችን ትናንትና እና ዛሬ ልካለች።
ሰሜን ኮሪያ ለጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ “ልባዊ ስጦታ” በሚል በተገለጸው ስጦታ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን የላከች ሲሆን፤ የጃፓን የስጦታ ድርሻ ደግሞ የአጭር ርቀት ባላስቲክ ሚሳዔሎች ናቸው ተብሏል።
የጃፓን መንግስት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፤ ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት የባላስቲክ ሚሳዔል ይሆናል ተብሎ የተገመተ መሳሪያ እንደተኮሰች አስታውቋል።
የአጭር ርቀት የባላስቲክ ሚሳዔሎቹ የጃፓን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተብሎ በተከለለው የባህር ክፍል አቅራቢያ መውደቃቸውን የጃፓን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አስታውቀዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየትም፤ ሰሜን ኮሪያ በአንድ ጊዜ በርካታ የአጭር ርቀት የባላስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ምስራቅ የባህር ክፍል ተኩሳለች።
የደቡብ ኮሪያ የጋራ የጦር አዛዥ በሰጡት አስተያየትም፤ ሰሜን ኮሪያ ወደ 10 የሚጠጉ የአጭር ርቀት የባላስቲክ ሚሳዔሎች ወደ ኮሪያ የባህር ጠረፎች ተተኩሰዋል።
ሚሳዔሎቹ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ አየር ላይ ከተጓዙ በኋላ የጃፓን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተብሎ በተከለለው የባህር ክፍል አቅራቢያ መውደቃቸውን አስታውቀዋል።
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በሰጡት አስተያየት፤ “ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን መተኮሷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህግን ጣሰ ነው” ብለዋል።
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች